25
Oct
2021
ባንኩን በይፋ ስራ ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የቤት አቅርቦት እና ፍላጎትን ለማሟላት መንግስት የተለያዩ ተግባራትን በመንደፍ እየሰራ ይገኛል ።የጎህ ቤቶች ባንክ በከተማችን መከፈትም ለከተማው ነዋሪ የምስራች ነው ብለዋል።
የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመፍታት መንግስት ብቻውን በቂ አይደለም ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመኖሪያ ቤት ግንባታ ዘርፍ የሚሰማሩ እንደጎህ የቤቶች ባንክ እና መሰል የፋይናንስ ተቋማት ሊበራከቱ ይገባል ብለዋል።
ባንኩ ውጤታማ እንዲሆን እና የታለመለትን አላማ እንዲያሳካ የከተማ አስተዳደሩም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ከንቲባዋ አመልክተዋል ።
የጎህ ቤቶች ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አስማረ በበኩላቸው ከቤት ፋይናንስ ጋር በተያያዘ ያለውን ክፍተት በመረዳት መፍትሄ ለማምጣት የተቋቋመ የመጀመሪያው የግል ባንክ ነው ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን ቤት ለማደስ የጀመረውን እንቅስቃሴ ለማገዝም የ1.5ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል ።