ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዮኒኬሽን ቢሮ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

 

ታህሳሰ 02/04/0214 ዓ.ም

አዲስ አበባ አትዮጵያ

1. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአስር ክፍለ ከተሞች በተደረገ የመሬት ዳሰሳ ጥናት 560.233.00 ካሬ መሬቶች በህገወጥ መንገድ የተወረሩ መሬቶች

በፍርድ ቤት እግድ ምክንያት ወደ መሬት ባንከ ገቢ እንዳይሆኑ እንዲሁም ለልማት እንዳይውሉ መቸገሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።

በፍርድ ቤት እግድ ምክንያት ህገወጥ መሬቶችን ወደ መሬት ባንክ መመለስ አልቻልንም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በፍርድ ቤት የመሬት እግድ ላይ ያለውን ቅሬታ አስታወቀ። እነዚህ ቅሬታ የፈጠሩት መሬቶች ወደልማትም ሆነ ወደ መሬት ባንክ እንዳይመለሱ በፍርድ ቤት እግድ ምክንያት መሆኑ ደግሞ ችግሩ የገዘፈ እንዲሆን አድርጎታል።

በኦዲት ግኝቱ መሰረት ፍርድ ቤት እግድ የጣለባቸው ምንም አይነት የልማት ተግባር ያልተከናወነባቸው ባዶ መሬቶችንም ጨምሮ ሲሆን። እግድ የተሰጣቸው ሰዎችም ምንም አይነት የባለመብትነት መረጃም ሆነ ማስረጃ የሌላቸው መሆኑን ከኦዲት ሪፖርቱ ማረጋገጥ ተቸሏል።

ሕግና ስርዓት የማስከበር ስራችን ህገወጥ የመሬት ወረራን ጨምሮ መተግበር አለበት ብሎ ከተማ አስተዳደሩ በጽኑ ስለሚያምን ጉዳዮ የሚመለከታቸው አካላት ህግና ስርዓትን ተከትለው ሀላፊነት በተሞላው ሂደት ሊሰሩ ይገባል።

May be an image of text that says 'ከንቲባ ፅህፈት ቤት- አዲስ አበባ -OFFICE OF THE MAYOR ADDIS ABABA, ETHIOPIA'

 

Share this Post