ከአዲስ አበባ ከተማ የተውጣጡ ከ3ሺህ በላይ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል አሸኛኘት ተደረገላቸው ። "ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ"!! ከሁሉም ከፍለ ከተሞች የተውጣጡ ወጣ...

ከአዲስ አበባ ከተማ የተውጣጡ ከ3ሺህ በላይ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል አሸኛኘት ተደረገላቸው ። "ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ"!! ከሁሉም ከፍለ ከተሞች የተውጣጡ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል ባመለከቱት መሰረት አሸኛኘት በዛሬው ዕለት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቀነአ ያደታ ፣የሀገር ሽማግሌዎች እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት በመስቀል አደባባይ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል ። ወጣቶቹ ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው በአፋጣኝ ምላሽ በመስጠታቸው ታሪክ የማይረሳው አኩሪ ገድል ፈጽማችኃል በዚህም ምስጋና ይገባችኋል ሲሉ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በሽኝት መርሐግብር ላይ ገልጸዋል ። የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቀነዓ ያደታ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ ሰራዊቱን በገንዘብ ፣በቁሳቁስ እና በሌሎች ተግባራት ለማገዝ እያደረገ ያለው ሁሉን ዓቀፍ ድጋፍ ሰራዊቱን የሚያበረታታ መሆኑን አብራርተዋል ። በዕለቱም ወጣቶቹ ከምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ከመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቀነዓ ያደታ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ተረከቡ ሲሆን የሀገር ሽማግሌዎች፣ እናቶች እና አባት አርበኞች ልጆቻቸውን በታላቅ ወኔ አበረታተዉ መርቀው ሸኝቷቸዋል።

Share this Post