ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የሰጠው ማሳሰቢያ የፖሊስ አባላት ሳይሆኑ ፖሊስ ወይም የፀጥታ አካላት ነን በማለት በተለያዩ ጊዜያት ወደ ንፁሃን ዜጎች ስልክ በመደወል የዛቻ ወንጀል የሚፈፅሙና የ...

ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የሰጠው ማሳሰቢያ የፖሊስ አባላት ሳይሆኑ ፖሊስ ወይም የፀጥታ አካላት ነን በማለት በተለያዩ ጊዜያት ወደ ንፁሃን ዜጎች ስልክ በመደወል የዛቻ ወንጀል የሚፈፅሙና የሚያስፈራሩ ግለሰቦች እንዳሉ የፌደራል ፖሊስ ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ህግ የማስከበር ተግባር እያከናወነ መሆኑም ይታወቃል። ሆኖም የፖሊስ አባላት ሳይሆኑ ፖሊስ ወይም የፀጥታ አካላት ነን በማለት በተለያዩ ጊዜያት ወደ ንፁሃን ዜጎች ስልክ በመደወል የዛቻ ወንጀል የሚፈፅሙና የሚያስፈራሩ ግለሰቦች እንዳሉ ነው ፖሊስ ያስታወቀው። በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የፌደራል፣ የክልልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰዉ፣ሀሰተኛ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመያዝ ህገ-ወጥ ብርበራና የዝርፊያ ሙከራ የሚፈጽሙ እንዳሉ ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ ጨማሪ መረጃዎችንም ማሰባሰቡንም ገልጿል። እንደነዚህ ዓይነት ድርጊት የተፈፀመባቸው ግለሰቦች ወይም በቀጣይ ተመሳሳይ ሁኔታ ከህግና አሰራር ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሲያጋጥም ድርጊቱ ህገ-ወጥ ስለሆነና በአሸባሪው ህወሃት ቡድን ርዝራዦች ሊፈፀም ስለሚችል ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል። በመሆኑም ህብረተሰቡ መሰልድርጊቶች ስያጋጥሙት በተቋሙ የስልክ መስመሮች ፈጥኖ በመደወል ህገ-ወጥ ግለሰቦችን ለህግ አቅርቦ ተጠያቂ ለማድረግና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ለሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንድያደርግ የፌዴራል ፖሊስ ጠይቋል። የስልክ መስመሮቹ፡-  ነፃ የስልክ መስመሮች 987፣ 816 እና 991, (አዲስ አበባ ፖሊስ)  ለወንጀል መከላከል ስልክ ቁጥር 0115524077  ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ የቢሮ ስልክ ቁጥሮች 0115309027 ፣0115309231 እና 0115309077  አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቢሮ ስልክ ቁጥር 0111110111 ናቸው።

Share this Post