የኮሙዩኒኬሽን እና የመገኛኛ መሳሪያዎች በእጁ የሚገኝ ማንኛዉም ግለሰብበ እንዲሁም ተቋማት በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እንዲያሳዉቁ ጥሪ ቀረበ
ሃገራችን ኢትዮጵያ የህልዉና ዘመቻ ላይ መሆኗ የሚታውቅ ነዉ። በዚህም በኢትዮጵያ ህልዉና አደጋን ለመከላከል፣ የተደቀነባትን የግዛት አንድነት ስጋት እና ሉአላዊነት ጥሰት ለመከላከል ሁሉን አቀፍ የጥንቃቄ እርምጃዎች መዉስድ አስፈላጊ ሆኗል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲም በአዋጅ በተሰጠዉ ስልጣን እና ሃላፊነት መሰረት በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የኢንፎርሜሽን እና የኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎችን ሲመዘግብ እና ሲቆጣጠር የቆየ ቢሆንም አሁናዊ ይዞታን ለማወቅ እና እነዚህ የኮሚዩኒኬሽን መሳሪያዎች በአሸባሪዎች እና ገብረ-አበሮቻቸዉ ለሽብር አላማ እንዳይዉሉ መሳሪያዎቹን እንደገና መመዝገብ እና በሚመለከተዉ አካል እጅ ስለመኖሩ ማወቅ ኤጀንሲዉ ተገቢ ሆኖ አግኝቶታል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮሙዩኒኬሽን እና የመገኛኛ መሳሪያዎች በእጁ የሚገኝ ማንኛዉም ግለሰብ፣ ተቋም፣ ኤምባሲ ወይም ዲፕሎማት፣ በመንግስታዊም ሆነ በግል ተቋማት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ አካላት፣ በዘርፉ የተሰማሩ አስመጪዎች እና ላኪዎች በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እንዲያሳዉቁ እናሳስባለን።
1. ወታደራዊ የቅኝት መሳሪያዎች
• የጦር ሜዳ መነጽር (binokular)
• ኮምፓስ (Compass)
• የጂፒኤስ መሳሪያ (GPS)
2. ወታደራዊ እና ሲቪል የመገናኛ መሳሪያዎች
• መገናኛ ሬዲዮ (Walkie Talkies radio)
• ሳተላይት ስልክ (satellite phone)
3. ቪሳት እና ቢጋን (A very small aperture terminal (VSAT) and Broadband Global Area network (BGAN))
4. ድሮኖች (Drones)
እነዚህን የመገናኛ እና ኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎች በግለሰቦች እጅ ወይም በተቋማት ውስጥ ሲጠቀም ያየ ማንኛዉም አካል ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጅንሲ በነጻ ስልክ ቁጥር 933 ወይም 0113851193 ፣ 0904049625 እና 0114701321 ማሳወቅ ይጠበቅበታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!