ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ምክር ቤት ውስጥ የስድስት ወር አፈፃፀም ያነሷቸው ነጥቦች የቀጠለ:-

 

👉 ትላልቅ (ሜጋ) ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈፃፀም በተመለከተ፤ ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ፤ በ19 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ተገንብቶ በቅርቡ የተመረቀው የአብርሆት ዘመናዊ ቤተ-መፃህፍት፤ በተቀመጠለት ጊዜና በጀት በፍጥነትም ሆነ በጥራት የመጨረስ አቅማችንን በድጋሚ ያረጋገጠ ትልቅ ፕሮጀክት ነው፡፡

👉 ከ57 አመት በላይ ያሰቆጠረው የመዘጋጃ ቤት ህንፃ፤ የቀድሞ ታሪካዊ ቅርፅን ሳይቀይር በ2.2 ቢሊዮን ብር የእድሳት ግንባታ ስራው ዘመናዊ ሆኖ ተጠናቆ ለምርቃት በቅቷል፡፡ይህ ታሪካዊና የከተማዋ ምልክት የሆነው የህንፃ እድሳት የከተማዋ የዘመናት ጉዞ አሻራ የያዘ ታላቅ ቅርስ ጭምር የሆነው ህንፃው ከተማዋ አለም ከደረሰበት የከተሞች እድገትና ውበትን በማላበስ ለተገልጋይ ምቹና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ሁሉ ባሟላ መንገድ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆንና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ተደርጐ በከፍተኛ ጥረት እድሳቱ ተጠናቋል።

👉 በ4.6 ቢሊዮን ብር በጀት እየተገነባ ያለው የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዝየም ፕሮጀክት፤ በግማሽ አመቱ የግንባታ አፈፃፀም 60% ከነበረበት ወደ 74.5% ማድረስ የተቻለ ሲሆን፤ የታላቁ ቤተ-መንግሥት የመኪና ማቆሚያ ግንባታ ከነበረበት 83% ወደ 85.1% ማድረስ ተችሏል፡፡

👉 በምግብ ዋስትና እና በልማታዊ ሴፍትኔት መርሃ ግብር 109 ሺህ 918 ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

👉 በመጀመሪያው ምዕራፍ በምግብ ዋስትና ተጠቃሚ የነበሩ 49,205 የቤተሰብ ኃላፊዎች ተመርቀው ወደ ዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም እንዲሸጋገሩ ማድረግ ተችሏል፡፡

👉 በየሳምንቱ የእሁድ ገበያን በተለያዩ የከተማዋ 14 ቦታዎች በማቅረብ እንዲሁም የመሰረታዊ ፍጆታ ሸቀጦች ለከተማ ነዋሪ በአነስተኛ ዋጋ በማቅረብ የኑሮ ውድነት ችግር ለማቃለል ተሞክሯል፡፡

👉 የአስተዳደሩ ካቢኔ ቀደምሲል ከተሰጠው 500 ሚሊየን ተዘዋዋሪ ብድር በተጨማሪ የ500 ሚሊዮን ብር ሪቮልቪይንግ ፈንድ መድቦ የሸማች ማህበራት የፋይናንስ ችግሮቻቸውን በማቃለል በህብረተሰቡ የሚደርሰውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና አቃሏል፡፡

👉 በተጨማሪም ለህብረተሰቡ በድጎማ የሚቀርበውን ዳቦ በስፋት ተደራሽ ለማድረግ ለሸገር ዳቦ ፋብሪካ 309 ሚሊዮን 337 ሺህ ብር ድጎማ ተደርጓል፡፡

👉 የመሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን አቅርቦት በተመለከተ ባለፉት ስድስት ወራት 508 ሺህ 912 ኩንታል ስኳር፤ 170 ሺህ 352 ጥሬ ስንዴ እና ከ12 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት ለሸማቹ ህብረተሰብ ማሰራጨት ተችሏል፡፡

👉 የከተማችንን ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ባደረግነው እንቅስቃሴ ለ899 የኢንቨስትመንት ፍቃድ ተሰጥቷል፡፡

👉 ገቢ ባለፉት ስድስት ወራት 26.53 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 31.45 (118.5%) ቢሊዮን ብር መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን፤ አፈፃፀም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 8 ቢሊዮን ብር ብልጫ ወይም በ35 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

👉 1.75 ቢሊዮን ብር በጀት እየተገነባ ያለው የትራንስፖርት ቢሮ (ጂ+20) ሕንፃ ግንባታ ከነበረበት 27.2% ወደ 35% እንዲሁም 1.4 ቢሊዮን ብር በጀት እየተገነባ ያለው የስልጠና ማእከል ግንባታ ከነበረበት 38% ወደ 40.5%ደርሷል፡፡

Share this Post