ወ/ሮ አዳነች አበቤ በወሎ ግንባር በመገኘት ድጋፍ አደረጉ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወሎ ግንባር በመገኘት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት 100 ሰንጋዎችን ጨምሮ ከ20 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዕለት ምግብ እና ሌሎች የአይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በወሎ ግንባር በሚገኙ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት እናንተ ለኢትዮጵያ ስትሉ ህይወታችሁን እየሰጣችሁ እና የኢትዮጵያን አንድነት ለመጠበቅ እየተፋለማችሁ ስለሆነ ውለታችሁ አለብን ብለዋል፡፡

ሀገር ለማፍረስ የመጣውን አሸባሪውን የህውሐት ቡድን ለመፋለም ብቻችሁን አይደላችሁም፤ ገንዘብ ብቻም አይደለም ህይወት ለመስጠት ዝግጁ ነን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።ዛሬ ይዘን የመጣነው ድጋፍ አብረናችሁ መሆናችንን ለማሳየት ነው ያሉት ከንቲባዋ በቀጣይም ለሰራዊቱ እና ቤተሰቦቻቸው አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሸንፋለች !

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

Share this Post