13
Dec
2021
“ዘመን ባስ” ከሸዋሮቢት፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ እና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች መነሻውን ከአዲስ አበባ አድርጎ ለ10 ቀናት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።በዛሬው እለትም ከሁለት አውቶብስ በላይ ተፈናቃዮች ተመዝግበው ነገ ጠዋት ጉዞ እንደሚጀምሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአቅመ ደካሞች፣ ለእናቶች እና ለህፃናት ቅድሚያ እንደሚሰጥ የገለፀው መረጃዉ መታወቂያ የያዘ ግለሰብ ከጠዋቱ 3 ሰአት ጀምሮ ላምበረት በሚገኘው መናህሪያ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል ታውቋል።አገልግሎቱን ለማግኘት በ“ዘመን ባስ” የትኬት መቁረጫ ቢሮዎች ሜክሲኮ፣ መስቀል አደባባይ እና እዛው ላምበረት መናህሪያ በሚገኙ ቢሮዎች መመዝገብ እንደሚቻልም ተገልጿል።