በአዲስ አበባ የሚገኙ የሴቶች አደረጃጀቶችና የምገባ ኤጀንሲ በጋራ ለመከላከያ ሠራዊት ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።
ወትሮም ቢሆን ጀግና የሆነው መከላከያ ሰራዊታችን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ መሪነት ድል በድል እሆነ ይገኛል ያሉት ከንቲባ አዳነች አበቤ ታሪክ የምናወራ ብቻ ሳንሆን ታሪካችን የሚወራ እየሆነ ነው ብለዋል፡፡ኢትዮጵያውያን ሰላም ፈላጊዎች ነን ፤ ለሰላም ቅድሚያ እንሰጣለን፤ ሰላማችን ሲነኩብን ግን ቀፎው እንደተነካ ንብ አንድ ሆነን ሰላማችንን እናረጋግጣለን ብለዋል፡፡እናቶች ከራስ በፊት ለሃገር ብላችሁ ካለችሁ ቀንሳችሁ ለመከላከያ ሰራዊታችን ያደረጋችሁት የገንዘብና ቁሳቁስ ድጋፍ አክብሮት የሚቸረው ተግባር ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
በከተማችን ውስጥ የሚገኙ ሴት አደረጃጀቶች እና በምገባ ኤጀንሲ ባለድርሻ አካላት ለመከላከያ ሰራዊቱ ደጀን በመሆን ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና የይገባችሃል ብለዋል፡፡በሶስተኛ ዙር ብቻ እስካሁን ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የገለጹት ከንቲባዋ አሁንም ድጋፉ ፥ በሁሉም ክ/ከተሞች የበሰሉ ምግቦች በማዘጋጀትም እስከ ግንባር የማቅረብ ስራ በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ ማርታ ሉዊጂ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያደረገ ያለው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ግንባር ካለው ወታደር የላቀ ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡