የህብረቱ ጉባኤ በመዲናችን መካሄድ አፍሪካውያን በእኛ ላይ ያላቸው እምነት ዛሬም ጽኑ መሆኑን እንደሚያሳይ ምሁራን ተናገሩ

 

35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በመዲናችን እንዲካሄድ መወሰናቸው የአፍሪካ ሀገራት በእኛ ላይ ያላቸው እምነት ዛሬም ጽኑ መሆኑን ያሳዩበት ነው ሲሉ ምሁራን ገለጹ፡፡የአፍሪካ መዲና ጭምር በሆነችው በአዲስ አበባ በመጪው ሳምንት የሚካሄደው የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ እንዲሳካ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ረገድ ካደረገችው ጥረት በተጨማ፥ ሪ አፍሪካውያን ወዳጆቻችን ያደረጉት ድጋፍ በእኛ ላይ ያላቸው እምነት የማይናወጥ መሆኑን ያሳዩበት ነው ብለዋል ምሁራኑ።

አንዳንድ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት በተቀናጀ መልኩ የሀሰት ወሬና ውዥንብር ሲያስወሩባት የቆየችው አገራችን ስብሰባውን በተለመደው መንገድ በሰላምና በመልካም መስተንግዶ እንድታስተናግድ መወሰናቸው የበለጠ አህጉራዊና ታሪካዊ ሃላፊነቷን በብቃት እንድትወጣ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ለቀጣይ የጋራ ጉዞም አበርክቶው የጎላ መሆኑን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር እና ተመራማሪው ዶክተር ፍሬው ይርጋለም እና ዶክተር መላኩ ተገኝ ተናግረዋል፡፡ለመድረኩ ስኬት ኢትዮጵያ የተጫወተችው ሚና ቢኖርም፥ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አገራችን ለአፍሪካ ነፃነት፣ አንድነትና ሰላም ያደረገችውን አስተዋጽኦ በሚመጥን ደረጃ ከጎኗ መሆናቸውን ያሳዩበት ውሳኔ ነው ብለዋል።

ከስብሰባው ጎን ለጎን የኢትዮጵያን እውነት በሚገባ ማስረዳት እና ለፓን አፍሪካኒዝምም አስተሳሰብ እንደገና ማበብ መሰረት መጣል ይገባል ነው ያሉትኑ።

የዚህን አህጉራዊ የመሪዎች ጉባኤ ለዓለም ህዝብ ለማድረስ የሚመጡት መገናኛ ብዙሃንን እና የመድረኩን ተሳታፊዎች ስለሀገራችን ነባራዊ ሁኔታና ትክክለኛ ገጽታ ለማሳወቅ በሚፈለገው ደረጃ በቂ መረጃዎችን ማስተላለፍ ይጠበቃል ብለዋል ምሁራኑ።

Share this Post