የልደታ ክ/ከተማ ያዘጋጀውን ስንቅ ድጋፍ በጣርማ በር ግንባር በመገኘት ለመከላከያ ሰራዊት አስረከበ።

 

የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮችና ተወካዮች በግንባር በመገኘት ድጋፉን አስረክበዋል።

የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰግደው ሀ/ጊዮርጊስ በድጋፍ አርክክቡ ወቅት እንደገለጹት መከላከያ ሰራዊቱ ለሀገር ሉዓላዊነት እንዲጠበቅ የምታደርጉት ተጋድሎና በአጭር ጊዜ ጠላትን ደምስሳቹህ ሰላማችንን እንዲረጋገጥ ሁሌም ከጎናችሁ አለን ብለዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ በበኩላቸው የኢትዮጲያ ህዝብ ቀፎው እንደተነካበት ንብ በአንድ ላይ ተነስቶ ከብረት የጠነከረ አንድነቱን በጠላት ትክሻ ላይ እያሳዬ ነው፤ ከተማ አስተዳደራችንም የህዝባችን ትብብር በማቀናጀት ለሰራዊታችን የሚያስፈልገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፋችንን እናጠናክረን እናስቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮለኔል ደጂሳ ህዝቡ እየሰጠን ያለው ፍቅር በግንባር ላይ ድል እንድናስመዘግብ ጉልበት ሆኖናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡ ጦርነቱን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅና የህዝባችንን ሰላም ለመመለስ በቁርጠኝነት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።ግንባር ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡት የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ሰላማችን እስከሚረጋገጥ ድረስ ድጋፋችን ይቀጥላል ብለዋል።

Share this Post