የመገናኛ ብዙሃን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትክክለኛ መረጃዎችን ለህዝብ በማድረስ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን /ቤት አዘጋጅነት "ሚዲያ ለሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ያለው ሚና "በሚል ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ከተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን /ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ ጸጋዬ ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ውስጣዊ እና ውጫዊ ጫናዎችን አስተናግዳለች ፤ይህን ጫና ለመቀልበስም በመንግስትና መገናኛ ብዙኃን የጋራ መግባባት ፈጥረው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

የመገናኛ ብዙሃን ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ከሚመለከታቸው አካላት በመቀበል ለህብረተሰቡ በማድረስ ለሀገራዊ አንድነት የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው አቶ አብዲ ገልጸዋል በውይይቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል መምህር / አብዲሳ ዘርዓይ ሚዲያ ለሀገረ መንግስት ግንባታ እና የቀውስ ጊዜ የተግባቦት ዙሪያ መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል

Share this Post