የኑሮ ዉድነትን ለመቀነስ "የእሁድ ገበያን" በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች መጀመራቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

 

ገበያዎቹ በየሳምንቱ እሁድ የተለያዩ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን ለከተማው ነዋሪ በአነስተኛ ዋጋ አሰንደሚቀርቡም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።

በዚህም በአምራቾችና በሸማቾች መካከል ቀጥተኛ እና አጭር የግብኝት ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ ይቻላል ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዋናነትም ህገ ወጥ የዋጋ ጭማሪና ሰዉ ሰራሽ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር አስቀድሞ መከላከል ያስችላል ብለዋል ።በሁሉም የከተማችን አቅጣጫ የምትገኙ ነዋሪዎች በእረፍት ቀናችሁ በአቅራቢያችሁ ወዳሉት የእሁድ ገበያዎች በመሄድ መገበያየት እንደሚችሉም አመልክተዋል ።

"የእሁድ ገበያን" በማስተባበር እና ሀሳብ በማመንጨት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ ባለድርሻ አካላት የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ብለዋል።

Share this Post