28
Jul
2021
የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ሲያካሂድ የነበረውን የ2013 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማውን ማምሻውን አጠናቋል ። ከጠዋት ጀምሮ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላትን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እና የተለያዩ ተቋማት አመራሮች በተገኙበት ሲካሄድ በነበረው የ2013 የስራ ዘመን የአበይት ተግባራት ስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ የበጀት አመቱ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ወይይት ተካሂዷል ። በበጀት ዓመቱም በየደረጃው ያለ አመራር ህብረተሰቡ ድረስ ወርዶ የመስራት ፣የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ፣ በገቢ አሰባሰብ ፣የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ፣ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የቦንድ ግዢ ፣የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እና በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ ህብረተሰቡን አስተባብሮ በማንቀሳቀስ ደሃ ተኮር በሆኑ የማህበራዊ ልማት ስራ...ዎችን በመስራት ረገድ የታየው በጎ ጅምር ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተገምግሟል ። ነዋሪዎች በዋናነት የሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ በተለይ በመሬት ልማት ማኔጅመንት ፣ በንግድ፣በትራንስፖርት ፣በግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ እና በመሳሰሉት ዘርፎች የሚስተዋሉ ቅሬታዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመወሰድ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ በዋናነት ተገልጿል ። በቀጣይም በተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ፣በተቋማት ግንባታና በመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ዙሪያ ፈጣን ምላሽ በመስጠት በሁሉም ደረጃ ተጠያቂነት ያለበትን አሰራር በማስፈን ረገድ በልዩ ትኩረት መስራት ይገባል ተብሏል ። ዛሬ የተጀመረው የ2013 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በቀጣይም እስከታችኛው መዋቅር ድረስ የሚቀጥል ይሆናል ።