የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቀንአ ያዴታ ወቅታዊ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታን አስመልክቶ ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥተዋል።

 

 

ኃላፊው በመግለጫቸው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጸጥታ ተቋማት ብሔራዊ ደሕንነትን ጨምሮ ከፌደራል የጸጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራቱ የከተማችን ሰላም ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል።በፀጥታ አካላትና ህብረተሰቡ ተሳትፎ በተደረገ ብርበራ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች ፣ለጥፋት ሊውሉ የነበሩ ከባንክ ሲስተም ዉጭ ያሉ የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ፣ልዩ ልዩ ወታደራዊ አልባሳት ፥ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል ሬንጀርን ጨምሮ፣ፎርጅድ መታወቂያዎች ፣የሕውኃትና ኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድኖች መታወቂያዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን ገልፀዋል ።የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለጸጥታ ኃይሉ መረጃ በመስጠት ፥ተደራጅቶ ስልጠና በመውሰድ አካባቢውን በቀንና በማታ በንቃት በመጠበቅ ላይ ይገኛል ::

የከተማው ነዋሪና የፀጥታ ሃይሉ ቅንጅት የሽብር ቡድኖች ፈጽመው እስኪወገዱ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል የቢሮ ኃላፊው።በከተማችን የተካሄደው የጦር መሣሪያ ምዝገባ መሣሪያው በማን እጅ እንዳለ ለማወቅና በተደራጀ መልኩ አካባቢን ከሌሎች ጋር ለመጠበቅ እንዲቻል ለማቀናጀት ነው።

ጊዚያዊ መታወቂያ የሚሰጥበት ዋና ምክንያትም ሰላማዊ ዜጎችን ከፀረ ሰላም ሃይሎች ለመለየት ስለሆነ በግልና የመንግሥት ተቋማት ጊዜያዊ መታወቂያ በመስጠት የሚስተዋለው ሕገ ወጥነት በሕግ የሚያስጠይቅና የአስቸኳይ ግዜ መመሪያዎችን መተላለፍ ነው ብለዋል።

ከተማችን ሙሉ በሙሉ ሰላሟ የተጠበቀ ነው ያሉት ዶ/ር ቀንአ ያዴታ ምዕራባዊን ሚዲያዎች ግን የተቀነባበረ የሽብር ቡድኖችን የመደገፍ ሴራቸው ለማስካት አዲስ አበባ ውስጥ የሽብር ጥቃት ሊከስት ይችላል እያሉ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻቸዉን ቀጥለውበታል ብለዋል ::

አሁን እየተደረገ ባለው ኦፕሬሽን ሌብነት በከተማችን ቀንሷል ሲሉም ገልፀዋል::የቢሮ ሃላፊው ወቅታዊ ሁኔታውን በመጠቀም የመሬት ወረራ ለማድረግ የሚሞክሩ አካላት እንዳሉ ጠቁመዋል። በዚህ ሕገ ወጥ ተግባር ውስጥ የሚስተፉ ኣካላት ሕዝቡ ጥቆማ በመስጠት እንዲያጋልጥ አሳስበዋል ።ከአሜሪካ ጋር ሽብርተኝነትን በጋራ ለመከላከል የተፈራረመን ቢሆንም እነሱ ከዚሁ በተቃራኒ ፍላጎታቸውን ተንተርሰው እያሴሩ ነው ይሕንንም በተመለከተ ከኤምባሲው ጋር ተደጋጋሚ ወይይት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል ።

Share this Post