የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የአመራር ግንባታ መድረክ መካሄድ ጀመረ።

 

"መመረጥ - ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ " በሚል ርዕስ ለዚሁ አላማ የተዘጋጀ ሰነድ ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው።

የውይይት መድረኩ በዛሬው እለት የተጀመረ ሲሆን የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ እና ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ አስጀምረውታል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረኩ አላማና ፋይዳ ዙሪያ ለተሳታፊ አመራሮች ገለጻ የሰጡ ሲሆን አሁን በተጀመረው የአመራር ግንባታ አካሄድ ፓርቲው ብቁ አመራር እየገነባ የጠራ እሳቤ ይዞ እንደሚወጣ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ የውይይት መድረኩ አላማና አካሄድን አስመልክተው በሰጡት የማብራሪያ ገለፃ ዋና አላማው አመራር መገንባት ነው ብለዋል።ብልፅግና በምርጫ ያገኘው ድልን ሳይሆን ህዝብ የማገልገል ዕድልን መሆኑን የገለፁት ሃላፊው ይህን ሃላፊነት ለመወጣት የአገልጋይነት መንፈስ ተላብሶ አገራዊ ሃላፊነት በአግባቡ የሚወጣ አመራር ማብቃት ያስፈልጋል ብለዋል።የአመራር የተግባር ጥንካሬና የፓርቲ ስነ ምግባር ከፍ በማድረግ የእያንዳንዱ አመራር ጥንካሬ እየጎለበተ ድክመት የሚታረምበት መድረክ እንደሆም አስረድተዋል።በተጨማሪም በርካታ የህዝብ አገልግሎት እንደመኖራቸው መጠን አመራሩ ችግሮችን የመፍታት እና በቅንነት የማገልገል አቅም መፍጠር፣ እንዲሁም ሀገራዊ እና የፓርቲ ተልዕኮን በብቃት መወጣት የሚችል አመራር የሚፈጥር ሂደት አካል መሆኑን አቶ መለሰ አብራርተዋል።

Share this Post