የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለስልጣን ከላዳ ታክሲ ማህበር እና ኤልኔት ግሩፕ ጋር በመተባበር በጉለሌ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሶስት አቅመ ዳካማ ቤቶችን እድሳት ጀመሩ ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን መንግስቱ እና የላዳ ታክሲ ማህበራት እና ከኤልኔት ግሩፕ ድርጅት አመራሮች ጋር በመሆን 700ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ በጉለሌ እና አዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ሶስት የአቅመ ዳካማ ቤቶችን የማሳደስ ስራ አስጀምረዋል።የላዳ ታክሲ ማህበራቱ ከቤት እድሳቱ በተጨማሪ በችግር ውስጥ ያሉ ጧሪ ቀባሪ ያጡ አረጋዊያንን በዘላቂነት የመደገፍ እና የመንከባከብ ስራ ለመስራት ቃል ገብተዋል፡፡

 

Share this Post