የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ288ሺህ እማወራና አባወራ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የ144 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

 

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ምዝገባና እድሳት ከጥቅምት 15 እስከ ህዳር 30 /2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ አስታውቋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ የማህበረሰብ ጤና መድህን በ2010 ዓ.ም በ10 ወረዳዎች ለ15ሺህ 8 መቶ 86 እማወራና አባወራዎች በፓይለት ደረጃ ወደ ስራ በመግባት ተገብቷል ብለዋል።በ2012 እና 13 ዓ.ም በሁሉም ወረዳዎች ተደራሽ በማድረግ የከተማውን ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የገለጹት ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ ከ231 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መድረግ ተችሏል ብለዋል።በዚህም የከተማ አስተዳደሩ ከ29 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ በማድረግ ህብረተሰቡ በነጻ እንዲታከም ማድረጉንም ሃላፊው ገልጸዋል ፡፡

በዘንድሮው 2014 አመትም የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ለማህበራዊ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት ለ288ሺህ እማወራና አባወራ በጠቅላላው ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የ144 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በማድረጉን ዶክተር ዮሐንስ ተናግረዋል ።ህብረተሰቡም ይህንን ከግምት በማስገባት የማህበረሰብ ጤና መድህን ምዝገባና እድሳት ከጥቅምት 15 እስከ ህዳር 30 /2014 ዓ.ም ድረስ በየወረዳው እንዲመዘገብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ኃላፊው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

Share this Post