የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦር ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የቁም እንስሳትና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

 

ግንባሩ ላይ ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የወገን ጦር በሠራችሁት ጀብድ ኮርተንባችኋል ብለዋል።ወደ ግንባር ስንመጣ ታላቅ ተጋድሎ የተፈጸመበት የጭና ተራራን ተመልክተን ፈርጣማ ክንዳችሁን በጠላት ላይ እንዳሳረፋችሁበትና አኩሪ ድል እንደተገኘ ለመገንዘብ ችለናል ብለዋል ከንቲባ አዳነች።

አሁን በድል ላይ ድል የሚመዘገብበት፤ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ሃይል ዳግም ሕዝብን መበደልም ሆነ መዝረፍ በማይችልበት ምእራፍ ላይ ደርሷል ነው ያሉት።"ጀግኖቻችን ክንዳችሁን በየ ግንባሩ እያሳያችሁ ኢትዮጵያ አንገቷን ቀና እንድታደርግና ነጻነቷን ጠብቃ እንድትኖር እያደረጋችሁ ነው" ብለዋል።"በቅርብ ቀን የህልውና ዘመቻውን በድል አጠናቅቀን በጋራ እጅ ለእጅ ተያይዘን የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር በጠላት መቃብር ላይ ቆመን እንዘምራለን" ብለዋል።ዛሬም ሆነ ነገ ኢትዮጵያን አሸናፊ የሚያደርጋት የእርስ በርስ ትብብር እንደሆነ ያስገንዘቡት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁሌም ከሠራዊቱ ጎን መሆኑንም ገልጸዋል።

በድጋፉ ላይ የተገኙት የማይፀብሪ ግምባር አስተባባሪው አገኘሁ ተሻገር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የአዲስ አበባ ሕዝብ ጠንካራ የሠራዊቱ ደጀን ነው፥ የከተማ አስተዳደሩና የሥራ ኀላፊዎች እያደረጉ የሚገኙት ድጋፍ በታሪክ ተመዝግቦ ይቀመጣል ብለዋል ።በተለይም ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የወራሪውን ቡድን የበሬ ወለደ ሀሰተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ፊት ለ ፊት በመጋፈጥና በማጋለጥ እያደረጉት ያለዉ ትግል ሁላችንንም የሚያኮራ ነዉ ብለዋል።በማይፀብሪ ግምባር የ24ኛ ቴዎድሮስ ክፍለጦር አዛዥ የሆኑት ኮረኔል ንጉሴ ለዉጤ በሰራዊቱ ስም የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

Share this Post