የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከመገናኛ ብዙኃን አመራሮች ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ከተማ አቀፋዊ ጉዳዮች እንዲሁም በከተማዋ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አመራሮች እና የሚዲያ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ በመረጃ የበለጸገ ማህበረሰብ ለመፈጠር እና ለነዋሪዎች ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ ለማድረስ የከተማ አስተዳደሩ ቢሮው በአዲስ መልክ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል ።

በተለይ የከተማ አስተዳደሩ ነዋሪዎችን በማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ የመገናኛ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል ።የተሳሳተ መረጃዎችን በመለየት ማህበረሰቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲደርስው ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራም አቶ ዮናስ ዘውዴ አመልክተዋል ።

በተጨማሪም በተቋማት መካከል ባልተደራጀ መንገድ እየተካሄደ ያለውን የመረጃ ፍሰት በማስተካከል የተሳለጠና መልካም የኮሙኒኬሽን ተግባቦት እንዲኖር ይሰራል ብለዋል።በመድረኩም በከተማ አስተዳደሩ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን አመራሮች ቀርቦ ውይይት እየተካሄበት ነው ።

Share this Post