የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፉት ቀናት በከተማዋ የተከናወኑ ሀገራዊ መርሃግብሮች ደማቅ እና ስኬታማ ሆነው እንዲጠናቀቁ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ነዋሪዎች እና የጸጥታ አካላት ምስጋና አቀረቡ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል በዓል፣ የኢሬቻ በዓል እና የመንግስት መስረታ እና ተያያዥ መርሀግብሮች በብቃት እና ሀገራዊ ገጽታን ከፍ ባደረገ መልኩ መፈጸም እንደተቻለ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸዋል፡፡

በዓላቶቹ ደማቅ ፣ሰላማዊ እና ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በተሞላበት መንገድ ለዓለም ምሳሌ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የከተማዋ ነዋሪዎች ትልቅ ድርሻ ወስደዋል፤ለዚህም ምስጋናና ክብር ይገባችኃል ብለዋል፡፡

ነዋሪዎች ከተማዋን በማጽዳት ፣ በማሳመር አንዱ በዓል ተጠናቆ ለሌላ በዓል በማዘጋጀት በእንግዳ ተቀባይነት እና በጨዋነት ተግባር እንዲጠናቀቅ ማድረጋቸውን ከንቲባዋ ጠቁመዋል፡፡

በመንግስት ምስረታው እና የጠቅላይ ሚኒስትር በዓለ ሲመት ነዋሪዎች ከጠዋት ጀምሮ በነቂስ በመውጣት ለሀገር ፍቅር ፣የመረጠውን መንግስት ለማጽናት እና በመንግስት ላይ ያላቸውን ተስፋ በአደባባይ በመግለጽ በሰላም እንዲጠናቀቅ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ህዝባችን የጣለብን ኃላፊነት ከፍተኛ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህን ለመወጣትም ተገቢውን እቅድ አቅደን እንሰራለን ብለዋል፡፡

Share this Post