የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ወደ መከላከያ ሠራዊት እንዲቀላቀሉ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ። ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት “ውድ የኢት...

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ወደ መከላከያ ሠራዊት እንዲቀላቀሉ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ። ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት “ውድ የኢትዮጵያ መዲና የአዲስ አበባ ወጣቶች እስካሁን ጀግናውን የመከላከያ ሰራዊታቻንን ለመቀላቀል የተመዘገባችሁና ገና ያልተመዘገባችሁ ፍጠኑ ከወንድሞቻችሁና ከእህቶቻችሁ ጋር ተሰለፉ” ሲሉ ጠይቀዋል። በመላ ሀገሪቱ ወጣቶች በትናንትናው ዕለት በሀገር ላይ የታወጀውን ሴራ ለመመከት ለቀረበላቸው ጥሪ የሰጡት ምላሽ የሚያስመሰግን መሆኑንም አውስተዋል። “የጀግኖች አባቶቻችን የሀገር ፍቅር፣ የጀግንነት እና የአይበገሬነት ወኔ ዳግም በዚህ ትውልድ ይደምቃል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፥ የህወሓት ጁንታን አርቀን በመቅበር በሀገር ላይ የተከፈተውን የውክልና ጦርነት በድል እናጠናቅቀዋለን” ብለዋል፡፡

Share this Post