11
Oct
2021
"ተመራቂዎች ኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በጀመረችበት ወቅት መመረቃችሁ ድርብርብ ኃላፊነት እንዲኖርባችሁ አድርጓል":-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ 72ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ከ 6ሺህ በላይ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት በወዳጅነት ፓርክ አስመርቋል ።የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እና የዩኒቨርስቲው አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለተመራቂዎች ፣ ለተመራቂ ቤተሰቦችና ለዩኒቨርስቲው መምህራንና ሰራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክትም ተመራቂዎች ኢትዮጵያ የልጆቿን ሁለንተናዊ ድጋፍና መልካም አስተዋጽኦ በምትሻበት በዚህ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በጀመረችበት ወቅት መመረቃችሁ ድርብርብ ኃላፊነት እንዲኖርባችሁ አድርጓል ብለዋል።
በመሆኑም በምትሰማሩበት የስራ መስክና የህይወት መንገድ የአገራችሁን ፤ የህዝቦቿን ተጠቃሚነት እና ኑሮ መሻሻል ለማረጋገጥ በርትታችሁ እንድትሰሩ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡መጪው ጊዜ በመደበኛ ትምህርት ያካበታችሁትን እዉቀት በተግባር ምዕራፍ የምትገልጡበት እንዲሆን እመኛለሁም” ነው ብለዋል ከንቲባዋ።