03
Jan
2022
ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት የተለያዩ ዝግጅቶች በከተማችን አዲስ አበባ በድምቀት መከናወናቸውን የቀጠሉ ሲሆን ዛሬ ጠዋት የአብርሆት ቤተመፅሀፍት የተመረቀ መሆኑ ይታወሳል በአሁን ሰዓት ደግሞ በክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አማካኝነት የአፍሪካ ፓርክ እየተመረቀ ይገኛል።
የአሁኑን የአፍሪካ ፖርክን ጨምሮ የኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ፓርኮችንም ከዛሬ ጀምሮ ለህዝብ ክፍት በመሆን አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናል።
በቦታው የተለያዩ ታሪካዊ፣ ባህላዊና አገራዊ ዝግጅቶች ለጎብኚዎች እየቀረበ ሲሆን የመዝናኛ ፕሮግራሞችም ተዘጋጅተዋል።