የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አፈ ጉባኤ ክብርት ጌጢቱ ሲሳይ የመከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ወሰኑ። አፈ-ጉባኤዋ ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ ላባደር ክፍለ ጦር ኮምቦልቻ ብርጌድ ከተራ ተዋጊ እስከ...

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አፈ ጉባኤ ክብርት ጌጢቱ ሲሳይ የመከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ወሰኑ። አፈ-ጉባኤዋ ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ ላባደር ክፍለ ጦር ኮምቦልቻ ብርጌድ ከተራ ተዋጊ እስከ ውጊያ ኦፕሬተር፣ እንዲሁም እስከ 1992ዓ.ም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በተለያዩ ስራዎች የስራ ድርሻዎች አገልግለዋል፡፡ በነገው እለት ወደ ውጊያ ግንባር ጉዞ ለማድረግ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተናግረዋል፡፡ «ጁንታው እኛ እያለን ሀገር ለማፈራርስ ማሰቡ ትክክል ባለመሆኑና ልጆቼን ማሳደግ የምችለው ሀገር ሰላም ስትሆን በመሆኑ የሀገርን ጥሪ ተቀብያለሁ›› ያሉት አፈ-ጉባኤዋ ‹‹የሀገር ጥሪን ስቀበል ለመጪው ትውልድ ፍቅርን አስተምራለሁ›› ብለዋል፡፡ ለሀገራችን አንድነት ሁላችንም የተቀጣጠለውን የመከፋፈል እሳት ማጥፋት አለብን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የፅህፈት ቤቱ ባለሞያዎች የሀገሪቱንን ጥሪ ተቀብለው ወደ ውጊያ ግንባር ስለሚሄዱ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በመስጠት ሽኝት ማድረጋቸውን ከኮልፌ ክ/ከተማ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Share this Post