የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጣር ተሻሽሎ በወጣው መመሪያ

በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ ያለውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጣር ተሻሽሎ በወጣው መመሪያ ቁጥር 803/2013 የተከለከሉ ተግባራትና የተጣሉ ግዴታዎች

Description: 👉ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ቫይረሱ እንዳለበት እያወቀ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት፣ ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀል፣ ቫይረሱ ወደ ሌሎች ሰዎች ሊተላለፍ በሚችልበት ሁኔታ ከሌሎች ሰዎች ጋር መገናኘት የተከለከለ ነው፣

Description: 👉ማንኛውም ሰው ለሰላምታ በእጅ መጨባበጥ ወይም የእርስ በእርስ አካላዊ ንክኪ ማድረግ የተከለከለ ነው፣

Description: 👉እድሜያቸው 6 አመት በታች ከሆኑ ህፃናትና በማሰረጃ የተረጋገጠ የመተንፈሻ አካላት ችግር ካለባቸው ሰዎች በስተቀር በማንኛውም ቦታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ መገኘት ወይም መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፣

Description: 👉በማንኛውም የመንግስትና የግል ተቋም ሰራተኞችና ተገልጋዮች ከሁለት የአዋቂ እርምጃ በታች ተጠጋግተው፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ አገልግሎት እንዲሰጡ ወይም እንዲያገኙ ማድረግ ወይም በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዲቀመጡ ማድረግ የተከለከለ ነው፣

Description: 👉በክፍት ገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው

Description: 👉ከሁለት የአዋቂ እርምጃ በታች ርቀት መቆምም ሆነ መቀመጥ የተከለከለ ነው፣

Description: 👉ማንኛውም የመንግስታዊ እና የግል ተቋማት ለሰራተኞች ስለ በሽታው አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣ በመግቢያና መውጫ በሮችና ሌሎች አስፈላጊ ቦታዎች በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን የማዘጋጀት፣ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን ማቅረብ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውንና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ግዴታ እንዳለባቸው መመሪያው ያዛል።

Share this Post