ያለፈዉን ታሪክ ብቻ የምናወድስ ሳንሆን የራሳችንን ታሪክ የምንፅፍ ትዉልዶች መሆን እንድንችል ስላረጋችሁን ኮርተንባችኋል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቢሾፍቱ ሜካናይዝድ የመከላከያ ኮምፕሬሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት የአካል ጉዳት የደረሰባቸዉን የሰራዊት አባላት ምግብ በመመገብ አጋርነታቸዉን አሳይተዋል፡፡

ከሁሉም በላይ እኛ እያለን አገራችን አትፈርስም፤ ሉዓላዊነታችን አይደፈርም በማለት ጠላትን ፊት ለፊት ተጋፍጠዉ ዋጋ በመክፈል ታሪክ የማይረሳዉ የጀግንነት ታሪክ የፈፀሙ ጀግኖች መካከል መሆን ያኮራል ብለዋል ከንቲባዋ ባደረጉት ንግግር ፡፡

ጀግኖቹ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የአባቶቻችንን ታሪክ ብቻ የምናወድስ ሳንሆን የራሳችንን ታሪክ የምንፅፍ ትዉልዶች በመሆን ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ታሪክ እንድንፅፍ አድርጋችሁናልና ክብር ይገባችኋል ብለዋል፡ከዚህ ቀደም ለመጀመሪያ ጊዜ ስመጣ ያገኘዋቸዉ ታካሚዎች አገግመዉ ግብአተመሬቱን ጀምረዉት የነበረዉን አሸባሪ ቡድን እስከወዲያኛው ለመቅበር ወደ ግምባር መሄዳቸውን ስሰማ እጅግ ኮርቻለሁ ነዉ ያሉት ።

ለሰራዊቲ የሚደረገዉ የደጀንነት ሁለንተናዊ ድጋፍ ለአገር ሉዓላዊነትና ለአገር ክብር የሚደረግ በመሆኑ ያኮራናል ዋነኛው የከተማችን አስተዳደር አጀንዳም ነዉ ሲሉ ገልጸዋል ከንቲባዋ፡፡አሁን ያለው የመከላከያ ሰራዊት የአገሪቷ መሪ ፊት ለፊት በግንባር ሆኖ የሚያዋጋዉ ሰራዊት በመሆኑ እድለኛና ታሪካዊ ሰራዊት ነዉ ብለዋል፡፡

ጠላት በአዉደ ዉጊያ እየተሸነፈ ነዉ ያሉት ከንቲባዋ የከተማ አስተዳደሩ ጀግናዉን የመከላከያ ሰራዊት የመደገፍ ስራዉን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

Share this Post