ፀረ ሰላም በሆነዉ እብሪተኛ ስብስብ የተቃጣብንን አደጋ መቀልበስ ከሁላችንም ይጠበቃል " ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

የተጋረጠባትን የህልዉና አደጋ በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ሉአላዊነቷን በማረጋገጥ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር አገር ባቀረበችው ጥሪ ሁሉ በግምባር መሰለፍ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ ።በኢትዮጵያ መፀሀፍ ቅዱስ ጥናት ማህበር አዘጋጅነት "ስለ አገራችን ሰላም ዕድገትና አንድነት በመተባበር እንስራ" በሚል መሪ መልዕክት በተካሄደዉ የዉይይትና የምክክር መድረክ መክፈቻ ላይ ነዉ ይህንን ያሉት ።

ሰላም የአገር መሰረት ነዉ ፤ ይህ እዉነት ከኢትዮጵያውያን የተደበቀ አይደለም ፤ ለሰላም ዋጋ ሲሉ ኢትዮጵያውን ብዙ ዋጋ ከፍለዋልም ነዉ ያሉት ።ስለ ሰላም እና አብሮነት ብለን የዘረጋነዉን የፍቅር እጅ ከመቀበል ይልቅ ዕብሪትና ማን አለብኝነት በተጠናወተው ቡድን ሰላሟን አጥታለች ፤ ይህንን ዕብሪተኛ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አደብ ለማስገዛትም ሲሉ መላው ኢትዮጵያን ከያሉበት በአንድነት ተነስተዋል ፤ ይህም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነዉ ብለዋል ።

አያይዘውም ሁሉም የሀይማኖት አባቶችና ተቋማት ጭምር ስለ ሰላም መፀለይ ፤ስለ ሰላም ማስተማር ፤ እንዲሁም ምዕመኑ የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅና በደጀንነት በመሰለፍ ረገድ ያለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት ማስገንዘብ ይገባቸዋል ብለዋል።

#አካባቢዎን ይጠብቁ!

#ወደ ግምባር ይዝመቱ!

#መከላከያን ይደግፉ!

Share this Post