የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ዛሬ ይካሄዳል


የ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በሚገኙበት ይካሄዳል።

በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ የመንግሥትን አቅጣጫ ዕቅድ የተመለከተ ንግግር እንደሚያሰሙ ይጠበቃል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ እንደሚገኙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ አመልክቷል።

Share this Post