አዲስ አበባ ህብረ-ብሔራዊት የሰላም እና የፍቅር ከተማ !!

ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (ማስ ስፖርት) ፕሮግራም ተከናወነ

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ //ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ ባስተላለፉት መልዕክት ስፖርት የግል ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር ለሰላም ያለው አስተዋጽኦ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ ጤናችንን እየጠበቅን የከተማችንን ሰላምና ልማት አጠናክረን መቀጠል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

በቤተሰብ ደረጃ የተጀመረውን "የሌማት ትሩፋት" ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ ሁለተኛ ዙር 90ቀን ልዩ እቅድ ይፋ ማድረጉን ያስታወሱት አቶ መለሰ ይህ እቅድ ከመደበኛ ስራዎቻችን ባሻገር ለብልፅግና ጉዞ ለምናደርገው ጥረት ልማታችንን የሚያፋጥን ስለሆነ ይህንን ፕሮግራም በዛሬው ዕለት በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በይፋ መጀመሩን አብስረዋል።

በዛሬው ዕለት በተከናወነው ከተማ አቀፍ ማስ ስፖርት ፕሮግራም የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን በቀጣይም በሌሎች ክፍለ ከተሞች ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

በፕሮግራሙ ላይ የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ //ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙን ጨምሮ የከተማ፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

Share this Post