በአዲስ አበባ ከተማ በህጻናት ላይ የሚደርሰውን አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ለማስቆም በተጀመረ የንቅናቄ ስራ ሁሉም የመንግስትና ሌሎች ባለድርሻዎች ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ፡፡

ምቹና ሰላማዊ ኢትዮጵያ ለሁሉም ህጻናት በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ላለው የዓለም አቀፍ የህጻናት ቀን የአዲስ አበባ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ከከተማ አስተዳደሩ ሴክተር ተቋማት አመራሮች ጋር የፓናል ውይይት አካሂዷል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ የሴቶች፣ ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ፤ኃላፊ ዶክተር ሃና የሺንጉስ እንዳሉት በከተማችን የአፈጻጸም ዘዴያቸውን እየቀያየሩ በህጻናት ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን ለመከላከል እና ለማስቆም ቢሮው የተለየዩ ሰራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት እየሰራ ከመሆኑም ሌላ ከህዳር 1/2015 ዓም ጀምሮ ቡና እንጠጣ ስለሴቶችና ህጻናት እናውጋ በሚልበ 595 ብሎኮች ከህዳር 5 እስከ 16/2015 የሚቆይ የችግሩን ምንጭ ለማድረቅ ንቅናቄ እየተፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡

የህጻናትን ጥቃቶችን ለማስቆም እንዲያስችል ማህበረሰቡን በውይይት ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ 11 ክፍለ ከተሞችና በሁሉም ወረዳዎች የጥቃት ተከላካይ ኮሚቴዎችን በማቋቋም እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመተባበር ነጻ የጥቃተት ጥቆማ የስልክ ጥሪ 991 አገልግሎት ላይ በማዋል እና ለተጎጂዎች ነጻ የጥብቅና አገልግት በመስጠት የፍትህ ሂደቱን ለመከታተልና የህክምና እና ስነ-ልቦና ምክር እንዲያገኙ በአራት ሆስፒታሎች የአንድ ማዕቀፍ አገለልግሎት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው በህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ማስቆም ባለመቻሉ ንቅናቄው መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

በዓለምአቀፍ 33 በሀገር አቀፍ 17 ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የህጻናት ቀንን አስመልክቶ ከመንግስት አመራሮች ጋር በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ የህጻናትን ጥቃት ለማስቆም መሰራት ስለሚገባው ስራዎች የሚገልጽ የመወያያ ሰነድ በሴቶችና ህጻናት ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ የቀረበ ሲሆን በሰነዱ መነሻ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በህጻናት ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ ጥሰት አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት ከምንጫቸው እንዲደርቁ ሁሉም የእቅዱ አካል አድርጎ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

ጥቃትን መከላከል በአንድ ተቋም ብቻ ላይ የምንተወው ሳይሆን በማህበረሰቡ ሚዲያዎችም ሆነ የመንግስት ተቋማት አሳታፊ ርብርብ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋልለ፡፡

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ሴክተር ተቋማት አመራሮችና የሚመለከታቸው ሌሎች ባለድርሻዎች ተሳታፊ የሆኑበት የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡

Share this Post