27
Nov
2022
***
1ኛ ሀቢባ ኡመር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ
2ኛ ተስፋዬ ግርማ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ
3ኛ በቃሉ ፀደቀ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት አስተዳደር ባለሙያ
4ኛ ጭምዴሳ ፉለአ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ባለሙያ እንዲሁም
5ኛ ልኡል ተረፈ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው እየሰሩ በነበረበት ወቅት ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅተው የመንግስት እና የህዝብ መሬት እንዲመዘበር በማድረጋቸው በተጠረጠሩበት ወንጀል በህግ ይፈለጋሉ፡፡
እነዚህ ግለሰቦች ያሉበትን የሚያውቅ ወይም መረጃ ያለው ማንኛውም ግለሰብ በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም አዲስ አበባ ፖሊስ በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 991፣ 0111110111 እና 0111568311 መረጃ በመስጠት የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡