31
Mar
2022
የአዲስ አበባ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ህገወጥ የውጭ ማስታዎቂያ ሰሌዳዎችን ማንሳት አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፣ 08፣ 10 እና 13 በህገ ወጥ መንገድ በመሰረተ ልማት አውታሮች እና የዋና መንገድ ኤልክትርክ ፖሎች ላይ የተሰቀሉ ህገ ወጥ የውጭ ማስታውቂያዎችን ማንሳቱን ገለፀ።
ከሳህሊተ ምህረት እስከ የተባበሩት በግራ እና ቀኝ መንገድ ፣ ከተባበሩት እስከ ፍየል ቤት እንዲሁም ከፍየል ቤት እስክ ፊጋ ወርዳ 08 እና 13 ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያዎች ተነስተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ወርዳ 10 ከተባበሩ እስከ አያት አደባባይ እና ከአያት አደባባይ እስከ ጣፎ አደባባይ ድረስ በግራና በቀኝ በኩል ተሰቅለው የነበሩ ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሙሉ በሙሉ ማንሳት የማንሳት ስራ ተከናውኗል።
በቀጣይም በሌሎች ክፍለ ከተሞች የተሰቀሉ ህገወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች የማንሳት ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለስልጣኑ ገልጿል።