የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ እና የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በአፍ መፍቻ ቋንቋና በአዲሱ ስርአተ ትምህርት ትግበራ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት አካሂዷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንደገለፁት አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወደ ማስተማሪያ ቋንቋዎች በመተርጎም የትምህርት ባለሙያዎችን የመለየት ሰራው ተሰርቷል ብለዋል፡፡
የአዲሱ ስርዓተ የትምህርት ትግበራን ስኬታማ ለማድረግ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች በጋር የልምድ ልውውጥ በማድረግ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ለማረጋገጥ የመምህራን ድርሻ የላቀ ነው ተብሏል፡፡
አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በከተማችን በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች የሙከራ ትግበራ እና የመፅሐፍ ዝግጅት 3 ነጥብ 9 ሚሊዮን መዘጋጀቱ እና እስከ አሁን 1ነጥብ 2 ሚሊዮን ኮፒ የማሰራጨቱ ስራ ተጠናቆ ወደ ተግባር መገባቱን በፓናል ውይይቱ በስፋት ቀረቧል፡፡
በፓናል ውይይቱም ተሳታፊዎች እንደተናገሩት በአዲሱ ሰርዓተ ትምህርት ዙሪያ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ለመምህራን በቂ የሆነ ግንዛቤ ባለመሰጠቱ ወጥ የሆነ የመማር ማስተማር ሂደት እንዳይኖር ማድረጉ ፤መፅሀፍቶች በጊዜው ተጠናቀው ለትምህርት ቤቶች ባለመድረሳቸው የመማር ማሳተማር ሂደት ላይ እንደ አንድ ችግር ሆኖ መገኘቱ በመድረኩ ተነስቷል፡፡
በመድረኩም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት አለማቀፍ ዕውቀቶችን የሚያመጣ እና ሀገራዊ ፈይዳውን የሚያጎላ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
የአዲሱ ሰርዓተ ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን በመውጣት ለሀገራችን የትምህርት ጥራት የበኩላቸውን ሀላፊነት መወጣት ያስፈልጋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ አሳስበዋል፡፡