የሴቶችና ማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

ቋሚ ኮሚቴው በዛሬው ውሎ የኮሙኒኬሽን ቢሮና የምገባ ኤጀንሲን ተመልክቷል።

ተቋማቱ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ከተቋማትና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተናቦና ተቀናጅቶ ከመስራት አንጻር በተለይ ከሚዲያ ተቋማት ጋር ተሳስሮ መስራት ላይ እንዲሁም በሌሎች መሰረታዊ ተግራት ጋር ተያይዞ በርካታ የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸው ተገልጿል።

በተመሳሳይ በምገባ ኤጀንሲም አበረታች ተግባራት ስለመከናወናቸው ቋሚ ኮሚቴው አመላክቷል።

በቀጣይም ከዚህ የተሻለ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባም ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።

ከእቅድ ጀምሮ የግብዓት የአደረጃጀት እና በሰው ሀብት ላይ ሰፋ ያሉ እጥረቶችና ውስንቶች ያሉባየው መሆኑ ታይቷል።

በቀጣይም እነዚህን ችግሮች በአጭር ጊዜ መቅረፍ እንደሚገባም ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።

 

Share this Post