"አራዳን እንደገና" የልማት ፕሮጀክቶች ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በተለያዩ የልማት ስራዎች ተጀመረ

የአራዳ /ከተማ አስተዳደር 90 ቀን ዕቅድ የሚሰሩ የአራዳን እንደገና የልማት ፕሮጀክቶችን የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙና ሌሎች የከተማና የክ/ከተማ እንዲሁም የወረዳ አመራሮች፣ የህዝብ ተመራጮች፣ ባለሀብቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት መሰረተ ድንጋይ በማስቀመጥ ተጀምሯል።

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት አራዳን እንደገና የልማት ፕሮጀክት የፓርቲያችን ጉባኤና የጠ/ / ዐብይን አቅጣጫዎች በመያዝ የህዝቡን አንገብጋቢ ችግር ለመመለስ እየተከናወኑ ካሉ 90 ቀን የልማት ፕሮጀክቶች አካል መሆኑን በመግለፅ ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውንና ገንዘባቸውን ለፕሮጀክቶቹ ስኬታማነት ለማዋል የቆረጡ ባለሀብቶችንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አመስግነዋል።

ፕሮጀክቶቹ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረጉ ሰው ተኮር መሆናቸውን የገለፁት ሀላፊው በተያዘላቸው ጊዜ በጥራትና በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሞላ ንጉስ በበኩላቸው በክ/ከተማው የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀው 90 ቀናት ዕቅድ ደግሞ ተጨማሪ የመልማት ዕድልን ስለሚፈጥር ለስኬታማነቱ መረባረብ ይገባል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት በተከናወነው የፕሮጀክቶች ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ በፕሮግራሙ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ በአጭር ጊዜ ተገንብው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች የሚተላለፉ ዘመናዊ ባለ ስድስት እና ባለ አራት ወለል ህንፃዎች ስራ ማስጀመር፣ 200 ቤቶች እድሳት ማስጀመር፣ መለስተኛ የእግር ኳስ ሜዳ፣ 21 የዳቦ ማከፋፈያና የአትክልት መሸጫ ሱቆች፣ መፀዳጃ ቤቶች ስራ የተጀመረ ሲሆን አንድ ሺህ የሚሆኑ ለሌማት ትሩፋቱ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ የዶሮ ማርቢያዎችም ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል።

Share this Post