የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ “ተጨባጭ እና ተግባራዊ” ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦችን እንዲያዘጋጅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠየቁ

17ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ተጨባጭ እና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦችን እንዲያዘጋጅ የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጠየቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ እያስተናገደች ባለችው ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸው የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ 17ኛው ኢንተርኔት አስተዳደር ጉባዔ አምስቱ ንኡስ መሪ ሃሳቦች ጋር በተጣጣመ ቁልፍ የዕድገት ጉዞዎች የታጀበ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ሽፋን በፈረንጆቹ 2017 ከነበረው 19 ሚሊየን ተጠቃሚዎች 2022 ወደ 30 ሚሊየን ከፍ ማለቱንም ተናግረዋል፡፡

4 ኔትወርክ ህዝብ በሚበዛባቸው ከተሞች እና 5 ኔትወርክን በትላልቅ ከተሞች መዘርጋቱ ግንኙነቱን እያፋጠነ ነው ብለዋል።

በመላ ሀገሪቱ 2 ሺህ300 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳላቸውም ተናግረዋል::

 

Share this Post