በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የታላቁ ቤተ መንግስት የመኪና ማቆምያ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተመርቋል።

 

ከ54,000 ካሬ ሜትር በሚበልጥ ቦታ ላይ ያረፈው፣ ባለብዙ አገልግሎት ሕንጻ 4 የምድር ቤት ወለሎች አሉት። በአንድ ጊዜ ከ1000 ለሚበልጡ ተሽከርካሪዎች ዘመናዊ ፣ ቀልጣፋ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት ይሰጣል። ለአካል ጉዳተኞችም ምቹ የሆኑ መተላለፊያዎችን አካትቷል።

ከመሬት በታች የሚገኘውና 105 ሜትር ርዝማኔ ያለው ዋሻ ወደ አንድነት ፓርክ ያመራል፣ ይህም ጎብኚዎች መኪናቸውን በምድር ቤት በሚገኘው የመኪና ማቆሚያ አቁመው መንገድ ማቋረጥ ሳይኖርባቸው ወደ አንድነት ፓርክ እንዲዘልቁ ያስችላል።

Share this Post