ሚድያ የህዝቦችን አንድነት ለማጠናከርና ቀጣይነት ላለው የነቃና የተደራጀ የህዝብ ተሳትፎ መጠቀም እንደሚገባ ተጠቆመ።

 

ለአዲስ አበባ ከተማ የሚድያና ኮሙኒኬሽን እመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ሚድያ የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች በስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽንና ዙርያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ባዘጋጀው በዚህ ስልጠና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነትን ጨምሮ የአዲስ አበባ ዮንቨርሲቲ ምሁራንና ሌሎች ባለሙያችም ስልጠናውን ለሚድያ ባለሙያዎቹ በመስጠት ተሳትፈዋል።

ስልጠናው በዲጂታል ዲፕሎማሲ ፤ በስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን፤ ሚድያ በአገር ግንባታና የህዝቦች አንድነት በመሳሰሉት ርእሶች ዙርያ እየተሰጠ ሲሆን ሚድያ የህዝቦችን አንድነት ለማጠናከርና ቀጣይነት ላለው የነቃና የተደራጀ የህዝብ ተሳትፎ መጠቀም እንደሚገባ በመድረኩ ተጠቁሟል።

Share this Post