የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ለኑሮ ውድነት ገፊ ምክንያቶች ዘላቂ መፍትሄው ማበጀት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት አካሂዷል።

 

በፓናል ውይይቱ ላይ ሸማች የህብረተሰብ ክፍሎች፥ የንግዱ ማሕበረሰብ አካላት ፥የሸማች ማሕበራት ፣ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ማለትም ንግድ ቢሮ የሕብረት ሥራ ኤጀንሲ ፣የከተማ ግብርና ኮሚሽን ፣የሐይማኖት ተቋማት ተወካዮች በፓናል ውይይቱ ላይ ተሳትፈው የየድርሻቸውን የመፍትሔ ሀሳብ ለቀጣይ ስራ ግብአት ይሆን ዘንድ አንጸባርቀዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት በምናከናውነው የፓናል ውይይት ለቀጣይ ስራ የሚረዱ በርካታ የመፍትሔ ሃሳቦች ይነሳሉ አምናለሁ ለዚህም የሁላችንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ለኑሮ ውድነቱን በሚፈለገው ፍጥነት መፍትሄ ለማበጀት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሚገባው እና በሚፈለገው ልክ የየድርሻችንን መወጣት ይገባል ብለዋል

Share this Post