19
Jan
2023
በዓሉ በአደባባይ በህብረት ደምቀን የምንታይበት የኢትዮጵያዊ አብሮነት ጥበቦች በህብረብሄራዊ ቀለማት አምረውና ተውበው የሚገለጡበት ፤ የእኛነታችን ጎልቶ የታየበት በዓል ነው፡፡
ከተማ አስተዳደራችን የጥምቀት በዓልን ውበትና ድምቀቱን በመጎናፀፍ ነዋሪዎቿ በጋራ ተሰባስበው የሚያሳልፉበት በርካታ የውጪ ቱሪስቶችን የምታስተናግድበት ፤በሁሉም አቅጣጫ እንደ አበባ ፈክታ ገፅታዋም የሚገነባበት እንዲሆን እንደጥምቀቱ እሴት ትህትናና አገልጋይነትን መተሳሰብና መከባበርን ተላብሰን ከእምነት አባቶች ጋር በጋራ ሰርተናል፡፡ ለዚህም ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡
ገና ብዙ ያልተሰራ የቤት ስራ አለብንና ከቂም ከጥላቻ፤ ከመከፋፈል ርቀን እጅ ለእጅ ተያይዘን ተግተን በመስራት መጪ ጊዜያችን ለሁላችም ብሩህ እናድርግ፡፡
በዓሉ ታሪካዊ እሴቱን ጠብቆ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ደምቆ እንዲከበር አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ አካላት ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ !
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ