የኮሙኒኬሽን ሙያተኞችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ መዋቅር ውስጥ ለሚሰሩ አራት መቶ ለሚሆኑ አመራር እና ሰራተኞች በዙር ተከፍሎ የሚሰጥ መሆኑ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገልጿል ።የኮሙኒኬሽን ሙያተኞችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ስልጠናው የሕዝብ ግንኙነት ሰነ ዘዴ፣የቀውስ ግዜ ጋዜጠኝነት ፣ዜና ትንታኔና ፊቸር አርትክል አዘገጃጀትን ማዕከል ባደረገ መልኩ በተጠቀሱ ጉዳዮች ዙሪያ የባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት ይሰጣል ተብሏል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሁሴን ዝናብ በመክፈቻው ወቅት እንደተናገሩት መንግሥትና ሕዝብን ማቀራረብ የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ኃላፊነት በመሆኑ በዚያው ልክ መስራትና ራስን ማብቃት ይገባል ብለዋል ።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው እንዳሉት በአሁኑ ወቅት ጽንፈኝነትን ማዕከል አድርገው መረጃ የሚያዛቡ አካላት በሕዝቦች መካከል ልዩነትን ለመፍጠር አበክረው እየሰሩ በመሆኑ የሀሰት መረጃዎቻቸውን በማጋለጥ ሚዛናዊ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ሁላችንም በተሰማራንበት የየድርሻችንን እንወጣ ብለዋል።

Share this Post