የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ የውጭ ማስታወቂያ ሙያዊ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ አሰጣጥና እና የይዘት ክትትልና ቁጥጥር መመሪያ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡፡

የውጭ ማስታወቂያ የሙያዊ ብቃት ማረጋገጫ በከተማው የሚስተዋሉ የማስታወቂያ ሰርዓቶችን አሁን ካለው ሰርዓት በተሻለ ደረጃ ለማሳደግ እና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የተዘጋጀ መመሪያ መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሙሴ አንበሴ መመሪያውን ያቀረቡ ሲሆን የውጭ ማስታወቂያ ሙያዊ ብቃት ማረጋገጫ መመሪያ በከተማችን ለሚስተዋሉ ችግሮች በአጭር ጊዜ ወደ መፍትሔ የሚያስገባ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሁሴን ዝናቡ እንደተናገሩት በውጭ ማስታወቂያ ሥራ የሚሰማሩ የማስታወቂያ ወኪል ወይም አሰራጮች የሙያዊ ብቃት ማረጋጫ ፍቃድ በማውጣት ሥራቸውን በህግ አግባብ እንዲያከናውኑ ለማድረግ እና ከማስታወቂያ አስነጋሪው ጋር መልካም የሆነ የሥራ ግንኙነት ለመፍጠር እና የማስታወቂያ ስርዓቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመቀየር መመሪያው ይረዳልም ብለዋል፡፡

አክለውም በውጪ ማስታወቂያ ማስተዋወቅ ሥራ የተሰማሩ የማስታወቂያ አሰራጮች አስነጋሪው እንዲሰራጭለት የሚፈልገውን ማስታወቂያ አግባብ ባለው ህግ የማህበረሰቡን መልካም ሥነ-ምግባር፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ እሴቶችን የሚያከብሩ የአገርን ክብርና ጥቅም የሚያስጠብቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

በውጭ ማስታወቂያ የተሰማሩ ተቋማትን በመመዝገብ ተገቢውን ክትትል፣ ድጋፍና ቁጥጥር ማድረግ በከተማዋ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካል የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ሊወጡ ይገባልም ተብሏል፡፡

Share this Post