እንኳን ለሴቶች ቀን አደረሰን! ሴትነት የመንፈስ ጥንካሬ ምልክት ነው:: ሴትነት የታማኝነት መገለጫ ነው:: ሴትነት ክብር ነው::

የዘንድሮውን የሴቶች ቀን ስናከብር በማያመች ሁኔታ ውስጥ ሆነው በስነምግባር የታነፀና ሃገሩን የሚወድ ትውልድ ለመገንባት ዋጋ የከፈሉ፣ ሳይማሩ ለልጆቻቸው የእውቀት ፀዳል የፈነጠቁ እንደ ሻማ ቀልጠው ለልጆቻቸው ብርሃን የሆኑ እንዲሁም የተሰጣቸውን ሃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ለትውልድ ህያው ምልክት እና ተምሳሌት የሆኑ መንፈሰ ጠንካራ ሴቶችን በማሰብ ነው::

የሴቶች ቀንን ስናከብር እለቱን ብቻ ሳይሆን በተለያየ ምክንያት ሴት እህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን ጫና እና ጥቃት በመቃወም በመታገል እንዲሁም ከጎናቸው በመቆም ጭምር ሊሆን ይገባል::

ዛሬ ላይ ያለን ሴቶች የተጀመረውን የትውልድ ግንባታ ራዕይ በማስቀጠል በራሳቸው የሚተማመኑ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶችን በመፍጠር ጠንካራ መሰረት ያላት እና የሴቶች ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚነት የተረጋገጠባት ሃገር ለመገንባት የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል::

በድጋሚ እንኳን ለሴቶች ቀን አደረሰን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Share this Post