የከተማችን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

 

“አካባቢየን በመጠበቅ ኃላፊነቴን እወጣለሁ” በሚል ሀሳብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት አካሄዷል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ በፓናል ውይይት መክፈቻው እንደተናገሩት የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ማስቻል ነው ያሉት ለዚህም ስኬታማነት የከተማችን ነዋሪዎች የጋራ ራዕይና ትብብር አስፈላጊ ነው ብለዋል ።

የቢሮ ኃላፊው አክለውም ሁላችንም ለሠላም ዋጋ በመስጠት የአካባቢያችንን ሁለንተናዊ ሠላም ለማረጋገጥ ከጸጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀንኣ ያዴታ በከተማችን መልካቸውን በመለዋወጥ የሚያጋጥሙ የወንጀል እንቅስቃሴዎችን በመከለከል ዘላቂ ሰላምና ደሕንነትን ለማረጋገጥ ከሕዝባችን ጋር በቅንጅት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

የፀጥታ ተቋማትን ሁለንተናዊ አቅም በማሳደግ ወንጀልና የደንብ ጥሰትን መከላከልና መቆጣጠር ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል ሃላፊው ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አራጋው መንግሥት በሁሉም ረገድ የፀጥታ ተቋማትን ወቅቱ በሚጠይቀው መልኩ ሪፎርም ለማድረግ መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ማህበረሰብ እቅፍ የፖሊስ ስራዎች ወንጀልን በመከላከል ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ማጠናከር ይገባል ተብሏል ::

ያለሕብረተሰቡ ተሳትፎ በዘላቂነት ሠላምን ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ ፤የከተማችን ነዋሪ ፖሊስ የሚፈልገውን የመረጃ ድጋፍ በመስጠት በአጋርነት መቆም ይጠበቅበታል ብለዋል ።

በፓናል ውይይቱ የሐይማኖት አባቶች ፣ወጣቶች ፣የብሎክ አደረጃጀት ተወካዮች ፣የፀጥታ አካላት፣ታወቂ ግለሰቦች ተሳትፈዋል።

Share this Post