ለህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ የኮሙኒኬሽን ስራዎችን በላቀ ኃላፊነት ማከናወን ይገባል ፦ እናትዓለም መለስ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

የከተማዋን የተግባቦት ስራ በቅንጅት እና በዕውቀት ለመምራት እንዲያስችል በአዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አዘጋጅነት ለመዋቅሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ።

በከተማ ደረጃ የኮሙዩኒኬሽን መዋቅሩን በማጠናከርና በተሳካ ሁኔታ በሕዝብና በመንግስት መካከል የሚኖርን ዘላቂ የመረጃ ልውውጥ ጤናማና ወቅቱን የጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል ብሎም በተዋረድ ቅንጅታዊ አሰራርን ለማስፈን የሚረዳ ሙያዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና በሁለት ዙሮች ለመዋቅሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሰጥቷል

በስልጠናው የመሪነት ተግባቦት ባህሪያትና ውጤታማነት፥ የቀውስ ግዜ ኮሙዩኒኬሽን ፣ስትራቴጂክ ኮሙዩኒኬሽን ፣ሃቅ የማጣራት ስነ ዘዴ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች በስፋት ተዳሰዋል።

የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ እናትዓለም መለስ በማጠቃለያው መድረክ ቀጣይ የስራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን በተለይም ስለህዝብ ሁለንተናዊ ደህንነትና ተጠቃሚነት መረጋገጥ የኮሙዩኒኬሽን ስራዎችን በላቀ ኃላፊነት ከማከናወን ባሻገር በመንግስትና በህዝብ መካከል ያሉ ፍላጎቶችንና የመረጃ ልውውጦችን በሰለጠነ መንገድ ወቅቱ በሚጠይቀው አግባብ ማከናወን ይገባል ብለዋል

የስትራቴጂክ ኮሙዩኒኬሽን መርህን በመከተል የመንግስት ፖሊሲና ቀጣይ የዕድገት አቅጣጫን በእውቀትና በእውነት ለሕዝብ በማስረዳት እንዲሁም እውነተኛና ሀሰተኛ መረጃዎችን በየግዜው በማጥራት ህዝባችን ከሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ተጽዕኖ የመታደግ ሃላፊነት ከሙያተኛው ይጠበቃል ብለዋል የቢሮ ኃላፊዋ

በአዲስ አበባ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ

/ ሜኤሶ ኤለማ በበኩላቸው የተደራጀና በአግባቡ ተልዕኮውን የሚያስፈጽም የኮሙዩኒኬሽን ሰራዊት በዘላቂነት በመገንባት በሁሉም ረገድ ያሉ የዕድገት አቅጣጫዎችና ግቦችን ሙያው በሚጠይቀው አግባብ በዘላቂነት ለህዝብ ተደራሽ ልናደርግ ይገባል ብለዋል

የጠላቶቻችን ፍላጎት ሀገራችን በቀጠናው መብቷንና ጥቅሟን የማታስከብር እንድትሆን ማድረግ ነው ያሉት ኃላፊው በእውነተኛና ወቅቱን በጠበቀ መረጃ እኩይ ዓላማቸውን በማጋለጥና ህዝቡን በማንቃት ለአገር አንድነትና ልማት ማንቀሳቀስ ይጠበቃል

Share this Post