ከተለያዩ የሐይማኖት አባቶች ጋር የአብሮነት ማዕድ የመቋደስ መርሃግብር ተደረገ።

 

የዛሬውንም የጋራ ማዕድ መቋደስ የምናደርገው የነበረውን የአብሮነት እሴታችንን ለማጽናት በማሰብ ነው ብለዋል በመርሃግብሩ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች፡፡

አምና ከሁሉም ዕምነት ተከታዮች ጋር በጋራ ማዕድ ተቋድሰናል ዛሬም ፈጣሪ ረድቶን በረመዳን ጾም ወቅት በጋራ የአብሮነት ማዕድ ለመቋደስ በቅተናል ያሉት ከንቲባ አዳነች ይህንን የአብሮነት እሴት አጠናክረን ማስቀጠል ይኖርብናል ብለዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አክለው ለኢትዮጵያችን ሠላም፣ለአንድነቷ መጸለይ ያስፈልጋል ብለዋል። የሐይማኖት አባቶች መቻቻል ፣አንድነት፤ መተሳሰብና ፍቅር በሕዝቦች መካከል እንዲኖር በርካታ ሥራዎችን ስትሰሩ ቆይታችኋል ለዚህም ከተማ አስተዳደሩ ታመስግናችኋለች ብለዋል፡፡

ሁላችንም ለሠላም ፤ ለልማትና አብሮነት አበክረን ልንሰራ ይገባል፤ ህብረታችን ጥንካሬያችን ነው፤መተሳሰባችን ጉልበታችን ነው ብለዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ለክርስትና እምነት ተከታዮች ለፋሲካ በዓል፤ ለእስልምና እምነት ተከታዮች ደግሞ ለረመዳን በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Share this Post