"የታሪካዊ ጠላቶቻችን እና የዉስጥ ባንዳዎች የጥፋት ሴራ እቅድ በሰላም ወዳዱ የከተማችን ነዋሪና በፀጥታ ሀይሉ ቅንጅት ከሽፏል!!"

 

በዛሬው እለትም ታላቁን የኢድ ሰላት ለማከናወን ህዝበ ሙስሊሙ በተሰባሰበበት ወቅት እኩይ ሴራቸውን ለመተግበር በሰማዕታት ሃዉልትና በመስቀል አደባባይ በተደረገ ሙከራ በንብረት እና በፀጥታ ሃይሎች ላይ መጠነኛ ጉዳት ቢደርስም በሰላም ወዳድ ሙስሊም ወገኖቻችን ብርቱ ጥረትና በፀጥታ ሃይሎች ቅንጅት የትርምስ ፍላጎቱና ዕቅድ ሙሉ ለሙሉ ከሽፏል ለዚህ እንኳን ደስ አላችሁ ።

ህዝበ ሙስሊሙም በሁሉም አካባቢዎች ሶላቱን ፈፅሞ ወደየአካባቢውና በሰላም ተመልሷል።

ወደፊትም በከተማችን አዲስ አበባና በመላው ሃገራችንን ሰላም ለማደፍረስና አንድነታችንን ለመበተን በሚፈልጉ የዉስጥ ባንዳዎችና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ላይ የማያዳግም እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ እናረጋግጣለን።"

Share this Post