የለውጥ መሳሪያዎችን በመጠቀም የአገልግሎት አሠጣጡን ለማዘመን ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ ።

 

አዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በማዕከል ፣ በሴክተሮችና በክፍለ ከተማ ደረጃ በመዋቅሩ ካሉ አመራሮችና ቡድን መሪዎችን በማሳተፍ ሲሰጥ የነበረው የBSC ስልጠና ተጠናቀቀ ::

የተቋማትን ስኬታማነት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች በቢ .ኤስ. ሲ አሠራር በመቃኘት፣ ክፍታቶችን በመለየት ፣ በማስልጠን፣ በመተግበር ፣ መሰራት እንደሚገባ የአዲስ ከተማ አሰተዳደር ኮሙኒኬሽን ምክትል ቢሮ ኃላፊ አብዲ ፀጋዬ ተናግረዋል።የተቋማትን ስትራቴጂንና አመታዊ እቅድን በማስተግበር ፣ ክፍያን ከውጤት ጋር ውጤትን ደግሞ ከአፈፃፀም ጋር በማስተሳሰር፣ ተቋማዊ መማማርን ዕውን ለማድረግ የBSC ስልጠናው ወሳኝ ነው።በመሆኑ የኮሙኒኬሽን ዘርፉ ትኩረት ሊሰጠው እንደ ሚገባ ምክትል ሃለፊው አስገንዝበዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ስልጠናው የተቋምን ስራዎች - አውቀን ቆጥሮ መስጠትና መቀበል መርህ ይዘን እንድንሰራ መሰረት የጣለ ነው ብለዋል።ቢሮውም በቀጣይ ተቋሙ በሁለንተናዊ ዘርፉ የአመራሩንና ባለሞያዎችን ብቃት ለማሳደግ በተከታታይነት እንደሚስራ ገልጿል።

 

 

Share this Post