09
Mar
2022
እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ በሚል መሪ ሃሳብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮና ከንቲባ ጽ/ቤት የሚሰሩ ሴቶች እና ተጋባዥ ባለድርሻ አካላት በጋራ በዓሉን አከበሩ::በመረሐ ግብሩ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ እስከ ወረዳ መዋቅር የሚገኙ ሴቶችና በከንቲባ ጽ/ቤት እንዲሁም በተጠሪ ተቋማት የሚሰሩ ሴቶች በጋራ ተደጋግፈው መሥራት በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የፓናል ውይይት አካሂደዋል፡፡
የፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች በከተማ አስተዳደሩ ከለውጡ ወዲህ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግና ሴቶችን በሁሉም ረገድ የበቁ ለማድረግ የተሰሩ ሥራዎችን በበጎ እንደሚመለከቱት ጠቅሰው፤ በሃገር አቀፍ ደረጃ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችንና ኋላ ቀር አመለካከቶችን ለማስወገድ ወንዶችን ያማከለ በሁሉም ረገድ የሚገለጽ ዘርፈ ብዙ ትግል ይጠይቃል ብለዋል ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ጽዮን ገብረማርያም በፓናል ውይይቱ ላይ እንደተናገሩት እኛ ሴቶች በመፈክር ብቻ የሚደገፍ ከእንችላለን ሃሳብ በዘለለ በተግባር በምንገኝበት የሥራ መስክ ሁሉ በተግባር ማረጋገጥ ይኖርብናል ሲሉ ገልጸዋል ።